ፍቅር………..

ፍቅር………..

ሌስ ብራውን ና ባለቤቱ በተመሳሳይ ቀን December 31, 1918 ነበር የተወለዱት፡፡ ሀይስኩል እንደተገናኙ ወዲያው ተዋደዱ፡፡ ሌስ ከሀብታም በቤተሰብ የተወለደ፤ ሄለን ደሞ ከዝቅተና ቤተሰብ የተወለዱ ነበሩ፡፡ ቤተሰቦቻቸውም አብሮነታቸውን አልወደዱም፡፡ ልክ 18 እንደሞላቸው ግን ተያይዘው ኮበለሉ፡፡

በደቡብ ካሊፎርኒያ ቤተሰብ መስርተው ኖሩ፡፡ እያንዳንዷን ቀናቸውን አብረው አሳልፈዋል፡፡ በ90ዎቹ እድሜያቸው እንኳን መልካም ግንኑነት የነበራቸው ጥንዶች ነበሩ፡፡

ወደ መጨረሻው ሄለን በሆድ ካንሰር ታመመች፤ ሌስም የፓርኪንሰን በሽታ ተጠቂ ሆነ፡፡ ከ75 አመት ትዳር በኋላ ሄለን July 10, 2013 ሞተች፡፡ ሌስ በቀጣዩ ቀን ተከተላት፡፡

ዴቪድ ኸርድ በ1907 ከጀማይካ ወደ ኒውዮርክ መጣ፡፡፡ ኑሮውን ለመደገፍ ያገኘውን ሁሉ እየሰራ በብቸኝነት ይኖር ነበር፡፡ ይህን ብቸኝነቱን ለማስታገስ ከወደ ካሪቢያን ለምትገኝ አቭሪል ለተባለች ሴት ደብዳቤ መፃፍ ጀመረ፡፡

በአመት ጊዜ ውስጥ ዴቪድ በአካል በማያውቃት ሴት ፍቅር ወደቀ፡፡ በእያንዳንዷ ደብዳቤ ልውውጥ ፍቅራቸው እየጨመረ ሄደ፡፡ ምንም እንኳን አይኑን አሳርፎባት ባያውቅም የጋብቻ ጥያቄውን በደብዳቤ ልኮ በጉጉት መጠበቅ ጀመረ፡፡ የአቭሪ ቤተሰቦች ይሁንታቸውን ሰጧት፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ የተያዩት ለሰርጋቸው ዴቪድ ወደ ጀማይካ በሄደ ጊዜ ነበር፡፡ በማግስቱ ተያይዘው ወደ ኒው ዮርክ በመሄድ ኑሯቸውን መሰረቱ፡፡ ስድስት ልጆችም ወለዱ፡፡

አቭሪል 1962 ከዚህ አለም በሞት ተለየች፡፡ ዴቪድ ሌላ ሚስት ሳያገባ ሌላም ሴት ሳይወድ 1971 ዘግይቶም ቢሆን ሚስቱን ተከተላት፡፡

በሀዊ ዳዲ

Did you find this post helpful? Share with your friends.