ሞትና ነፍስ

ሞትና ነፍስ

ሳይንስና ሳይንቲስቶች ነገሮችን ለመረዳት ብሎም ለማረጋገጥ ከዛም ጥቅም ላይ ለማዋል ሁሌም እንደዳከሩ ነው፡፡ ከነዚም ውስጥ አንዳንዶቹ እጅግ አነጋጋሪ አለፍ ሲልም አስቂኝ የሆኑ የሙከራ ስራዎችን ያከናውናሉ፡፡ እኔ፤ እነዚህ ሰዎች ውስጣቸው ያለው የታመቀ እውቀት ይች አለም ከምትይዘው ጋር አለመጣጠን ሲላቸው የሚፈጥሩት ትእይንት ነው እላለሁ፡፡ እናነተም ያሻችሁን በሉ፡፡ አሁን ግን እስከዛሬ ከተደረጉ ሳይንሳዊ ሙከራዎች መካከል በጣም አስገራሚ ሆነው ያገኘኋቸውን ሁለቱን እነሆ፡-

1.ሙት መቀስቀስ

የዚህ ሳይንሳዊ ሙከራው ባለቤት ሮበርት ኮርቢሽ ይባላል፡፡ ይህ ተመራማሪ ገና በልጅነታቸው ምጡቅ ለመባል ከበቁ ተመራማሪዎች አንዱ ነው፡፡ የዶክትሬት ዲግሪውን በ22 ዓመት እድሜው ማግኘቱ ለዚህ ምስክር ነው፡፡

በ1930ዎቹ ይህ ሰው ሙታንን ከሞት መመለስ እንደሚችል ያምን ነበር፡፡ ይህንንም እምነቱን ለማረጋገጥ ሙከራውን አከናውኗል፡፡፡

ሙከራውን የጀመረው በውሾች ላይ ሲሆን (በጊዜው በሰው ልጅ መሞከር አስቸጋሪ ስለነበር) የመጀመሪያ ሁለት ሙከራዎቹ ፍሬያማ አልነበሩም፡፡ ነነር ግን ሶስተኛና አራተኛ ሙከራው ላይ ሊሳካለት ችሏል፡፡፡

ለሙከራው የተጠቀማቸው ውሾች በመጀመሪያ በሳይንሳዊ ዘዴ ህይወታችው እንዲያልፍ አደረገ፡፡ ከመቀጠሉም በፊት ለ10 ደቂቃ ያህል አቆያቸው፡፡ በመቀጠል ወደላይ ወደታች አካላቸውን እያንቀሳቀሰ የደም ዝውውር ለመፍጠር ሞከረ፡፡ በእንቅስቃሴው መሃል የተለያዩ አይነት ሆርሞኖችና መድሀኒቶችን ወጋ፡፡

በዚሀው ሁኔታ 3ኛው ውሻ ከሞት መነሳት ችሏል፡፡ ያለ ችግር ግን አልነበረም፡፡ ውሻው የእይታና የጭንቅላት እክሎች ነበሩበት፡፡ ነገር ግን ከቀናት በኋላ በተወሰነ መልኩ አገግሟል፡፡

በዚህ ውጤቱ በመነሳሰት አራተኛውን ውሻ በ30 ደቂቃዎች ውስጥ ወደ ህይወት መመለስ ችሏል፡፡ ውሾቹም ለአንድ ወር አካባቢ በህይወት ቆይተዋል፡፡

ይህን አነጋጋሪ ምርምሩን በሰው ልጆች ላይ ለመሞከር እድሉን ሳያገኝ ነበር በ1963 ዓ.ም ለሞት የበቃው፡፡

2.የነፍሳችን ኪሎ

ይህ ሙከራ የተደረገው በሚያዝያ 10 1901ዓ.ም በዶ/ር ዱካን ነው፡፡ ዶ/ር ዱካን ነፍስ ክብደት እነዳለው ያምን ነበር፡፡ ይህን እምነቱን ወደ ሳይንስ ለማምጣት ሊሞቱ በደረሱ ሰዎች ላይ ሙከራውን ለማካሄድ ችሏል፡፡ ከ6ቱ ለሙከራ ከቀረቡ ሰዎች ውስጥ የአራቱን ውጤት ከአጋሮቹጋ በትክክል ተከታትለውታል፡፡ የክብደት ልኬቱ የተከናወነው ሟቾቹ በሚተኙበት አልጋ ላይ በተገጠመ መሳሪያ ነው፡፡

የመጀመሪያ ሰው ልክ እንደሞተ ሚዛኑ እንቅስቃሴ አሳይቷል፡፡ የቀነሰውም 21.2 ግራም አካባቢ ነው፡፡ የክብደት መጠኑ በተወሰነ ቢለያይም በአራቱም ሰዎች ላይ ተመሳሳይ ክስተት ተመዝግቧል፡፡

የተለየ ሁኔታ የታየው በሶስተኛው ሰው ላይ ሲሆን ሰውው ከመሞቱ 1 ደቂቃ ድረስ ምንም አይነት የክብደት ለውጥ አልፈጠረም፡፡ ልክ አንድ ደቂቃ ሲሞላው ከሌሎቹ ጋር ተቀራራቢነት ያለው ኪሎ ቀንሷልል፡፡ ዶ/ር ዱካን ይሄህን “እጅግ የተረጋጉ ሰዎች ሲሞቱ ነፍሳቸው ነፃነቷን ከማግኘቷ በፊት ከአካላቸው ጋር ተንጠልጥላ ትቆያለች” በማለት ለማብራራት ሞረዋል፡፡

ይህ የኪሎ ልዩነት እንግዲ የተለያዩ የፊዚክ መጠኖችንም ያካተተ ነው፡፡ (ለምሳሌ፡- የሚገባና የሚወጣ አየር) ተመራማሪዎቹ እነዚህን ውጤቶች በመቀነስ በአማካኝ የሰውልጅ ነፍስ 21 ግራም ይመዝናል ብለዋል፡፡

ይህን ተከትሎም ዶ/ር ዱካን በ15 ውሾች ላይ ሙከራ አካሂዷል፡፡ ነገር ግን ምንም አይነት የክብደት ለውጥ ሳይታይ ቀርቷል፡፡ በመሆኑም ነፍስ ያላቸው ሰዎች ብቻ ናቸው ይላል ዶ/ር ዱካን፡፡

www.madscientistblog.ca

ሀዊ ዳዲ

Did you find this post helpful? Share with your friends.