ኮምፒውተርዎ በቫይረስ ወይም በተለያዩ ማልዌሮች (Malware) መያዙን ማዎቅ የሚያስቸሉ 10 መንገዶች

ኮምፒውተርዎ በቫይረስ ወይም በተለያዩ ማልዌሮች (Malware) መያዙን ማዎቅ የሚያስቸሉ 10 መንገዶች

በሚከተሉት ምልክቶች ኮምፒውተርዎ በቫይረስ ወይም በተለያዩ ማልዌሮች (Malwares) መያዝ አለመያዙን ማረጋገጥ ይቸላሉ::

  1. ፕሮግራሞች አልከፈት ካሉ ወይም በአጋጣሚ ከጠፉ

አንዳንድ ፐሮግራሞቸ አንደ ታስክ ማናጀር (Task manager) አና ሬጀስተሪ አዲተር (Registry editor) የመሳሰሉ ፕሮግራሞች ያለመንም አሳማኝ መክንያት ከጠፉ::

  1. ያለተልመደ የኔትዎርክ መጨናነቅ

ኢንተርኔት የምንጠቀመባቸው ፕሮግራሞች (internet browser) አና የተለያዩ የኢንተርኔት ግንኙነት የሚፈልጉ ፕሮግራሞች ተዘግተው እያለ ኮምፕዩተርዎ የተለያዩ ያልተፈለጉ ፋይሎችን አሚያወርድ (download) ወይም እሚጭን (upload) ከሆነ ያለጥርጥር ኮምፒዉተርዎ በቫይረስ ተይዞአል ማለት ነው:: ከሚያወርዳቸው (download) ወይም አፕሎድ ከሚአደርጋቸው ፋይሎች ዉስጥ የተለያዩ ቫይረሶች (viruses) ሊዎርዱ ወይም የተለያዩ የግል መረጃዎች ሊጫኑ (upload) ይችላሉ::

  1. የኢንተርኔት ግንኙነት አልሰራም ካለ ወይም በጣም አሚዘገይ ከሆነ

በአጋጣሚ የኮምፒውተርዎ የኢንተርኔት ግንኙነት አልሰራ እያለ ካስቸገረ አና በጣም አሚዘገይ ከሆነ ኮምፒዉተርዎ በቫይረስ ተይዞ ሊሆን ይችላል ማለት ነው::

  1. በጣም አሚያሰለቹ ያልተፈለጉ ፕሮግራሞች በተደጋጋሚ አሚከፈቱ ከሆነ (annoying popups of unwanted programs) አና ወዳልተፈለጉ ደህረ-ገፆች (websites) የሚመራዎ ከሆነ

በኮምፒተርዎ ዉስጥ ያልተፈለጉ ፕሮግራሞች በተደጋጋሚ እሚከፈቱበት ቁጥር ከጨመረ ወይም ሊከፍቱት ከፈለጉት ደህረ-ገፅ ወዳልተፈለጉ ደህረ-ገፆች (websites) የሚመራዎ ከሆነ ኮምፒዉተርዎ በቫይረስ ተጠቅቷል ማለት ነው::

  1. ኮምፒዉተርዎ አልከፈትም ካለ

በአጋጣሚ የኮምፒውተርዎ ያለምንም ምክንያት አልከፈትም ካለ::

  1. ኮምፒዉተርዎ በጣም ከዘገየ

ያለ ምንም አሳማኝ መክንያት ኮምፒዉተርዎ በጣም ከዘገየ::

  1. የተለያዩ ፕሮግራሞች ማንም ሳይከፍታቸው በራሳቸው ጊዜ የሚከፈቱ ከሆነ

አንዳንድ ቫይረሶች በኮምፒዉተርዎ ዉስጥ የተለያዩ አደገኛና መጥፎ ፕሮግራሞችን ለራሳቸው የማስተዋወቂያ (advertisement) ሥራ አና ተጠቃሚዉን በአንዳንድ መልክቶች ለማስጠንቀቅ ይከፍታሉ::

  1. ያልተለመዱ የፋይል ጥምረቶች (unusual file associations)

ቫይረሶች በኮምፒዉተርዎ ዉስጥ የተለያዩ ፋይሎችን አንዳይከፈቱ ለማድረግ ወደ “.exe” የፋይል ጥምረት ወይም ወደ ሌሎች ጥምረቶች ይለዉጣሉ::

ለምሳሌ:- ለመክፈት የፈለግነው ፋይል ወርድ (word document) ቢሆን, የነበረው ዳታ(data) ጥምረት “.docx” ነው ግን በቫይረሶች ምክንያት ወደ “.exe” ይለወጣሉ::

  1. የሴኩርትይ ፕሮግራሞች መጥፋት

አብዛኞቹ የኮምፒዉተር ቫይረሶች የsecurity ፕሮግራሞችን ያጠፋሉ::

  1. በጣም አሰልች ፀባይ

ኮምፒዉተርዎ አሳይቶት የማያቀዉን የመረበሽ ፀባይ ካመጣ::

ምሳሌ:- አላሰፈላጊ e-mail መላክን ያካትታል

ማሳሰቢያ: አብዛኞቹ ቫይረሶች በአሪፍ antivirus ልናጠፋቸው አንችላለን

ከላይ የተጠቀሱትን ቸግሮች ለማስዎገድ የተመረጡ አንቲ-ቫይረሶች

Avast 
Smadav
Avira
Kaspersky

ተፃፈ – በዳዊት ሰለሞን

Did you find this post helpful? Share with your friends.