ኮምፒውተሮቻችንን ፈጣን እና ቀልጣፋ ማድረግ የሚያስችሉ 15 ነጥቦች

ኮምፒውተሮቻችንን ፈጣን እና ቀልጣፋ ማድረግ የሚያስችሉ 15 ነጥቦች

ኮምፒውተሮቻችንን በእለት ተእለት ስራዎቻችን እጅግ ጠቃሚ የሆኑ መሳሪያዎች ናቸው። እነዚህ አስፈላጊ መሳሪያዎች ብቃታቸው ሳይቀንስ እና ፈጣን ሆነው እንዲዘልቁ  ይጠቅማሉ  ያልናቸውን  15 ነጥቦች እነሆ፡

 1. የማያገለግሉ ፕሮግራሞች እና ሶፍትዌሮችን ማስወገድ

በኮምፒውተሩ ውስጥ ከሚገኙት ፕሮግራሞች እና ሶፍትዌሮች ለጊዜው የማያስፈልጉትን በመሰረዝ በኮምፒውተሩ ውስጥ  በቂ ክፍተት እና ቦታ በመተው የማሽኑን ስራ ማሳለጥ ይቻላል። በኮምፒውተሩ ውስጥ ከሚገኙት ፕሮግራሞች እና ሶፍትዌሮች ዝርዝር በሙሉ ኮንትሮል ፓናል ውስጥ የሚገኙ ሲሆን አላስፈላጊ ፕሮግራሞች በመለየት ማጥፋት ይቻላል።

computing2

 1. ፋይሎችን መደምሰስ

ኮምፒውተሮቻችንን በየጊዜው በተጠቀምንበት ቁጥር የተለያዩ አላስፈላጊ ፋይሎችን እየጨመርን እንሄዳለን የነዚህ ፋይሎች ክምችት ከጊዜ በኋላ ኮምፒውተሩን ቀርፋፋ ያደርጉታል። ስለዚህ በየጊዜው እነዚህን ፋይሎች መሰረዝ ይገባል።

 1. የኢንተርኔት ታሪኮችን እና አብረው የወረዱ ፋይሎችን ማስወገድ

ኢንተርኔት ታሪኮችን (Internet History) ማለት ኢንተርኔት መጠቀማችንን ተከትሎ በኮምፒውተሮቻችንን የሚቀሩ የተለያየ ፎርማት ያላቸው ዶክመንቶች ናቸው። እነዚህ ዶክመንቶች ኮምፒውተሮቻችንን ክፍት ቦታዎች በማጣበብ ኮምፒውተሮቻችንን ቀርፋፋ ከማድረግ በተጨማሪ የተለያዩ ማልዌሮችን ስለሚይዙ ኮምፒውተሮቻችንን ለሳይበር አታክ ተጋላጭ ያደርጉታል። በመሆኑም  ኢንተርኔት ከተጠቀምን በኋላ እነዚህን ፋይሎችን ማጥፋት ይገባል።

 1. ሃርድ ዲስክን ማ ጽዳት (Disk Cleanup)

ዲስክ ክሊን አፕ ማድረግ በC ረድፍ (C drive)   የሚገኙትን አላስፈላጊ ነገሮች በማስወገድ ኮምፒውተሮቻች ፈጣን ያደርግልናል። ይህንንም ለማድረግ የሚከተለውን መንገድ መከተል ይቻላል። Start menu>All programs>Accessories>System tools>Disk Cleanup

computing3

 1. ሪሳይክል ቢን መጠቀም
 2. አንቲ ቫይረስ (Anti-Virus) መጫን

አንቲ ቫይረስ (Antivirus) ኮምፒውተሮቻችንን ከየተለያዩ ማልዌሮች በመታደግ የኮምፒውተሮቻችንን ደህንነት የጠብቅልናል።ይህም ማሽኑን ሊያጠቁት ከሚችሉ ቫይረሶች በመታደግ ኮምፒውተራችን ስራውን በአግባቡ እንዲሰራ ያደርገዋል።

 1. ዲስክ ፍራግመንት (Disk Defragment) ማድረግ

ዲስክ ፍራግመንት (Disk Defragment) ማድረግ ኮምፒውተሩ በአግባቡ እንዲሰራ ይጠቅማል።. ይህንንም ለማድረግ ወደ ዲስክ በማምራት ራይት ክሊክ በማድረግ ፕሮፐርቲ በመጫን tool tab ላይ Defragment now የሚለውን በመምረጥ ማድረግ ይቻላል።

 1. የዲስክ ችግሮች እንዳሉ ማረጋገጥ

የዲስክ ችግሮች ኮምፒውተሮቻችንን ቀርፋፋ  ያደርጋሉ: የዲስክ ችግሮች እንዳሉ ለማረጋገጥ ወደ ዲስክ በማምራት ራይት ክሊክ በማድረግ ፕሮፐርቲ በመጫን tool tab ላይ check now የሚለውን በመምረጥ ማረጋገጥ ይቻላል።

computing4

 1. የዊንዶውስ ፕሮግራሞችን ማደስ

ማይክሮሶፍት ዊንዶው ለኮምፒውተር ፍጥነት የሚረዱ ፕሮግራሞች የሚይዝ ሲሆን ነገር ግን እነዚህ ፕሮግራሞች መታደስ ይኖርባቸዋል። እነዚህን ፕሮግራሞች  በማደስ (updateበማድረግ)  የኮምፒውተርን ፍጥነት መጨመር ይቻላል።

 1. ራም (RAM) መጨመር

አንዳንድ ጊዜ የኮምፒውተርን ፍጥነት ለመጨመር ተጨማሪ ራም መጨመር አስፈላጊ ነው። ከላይ የተገለጹት መፍትሄዎች በቂ ሆነው ካልተገኙ ራም በመጨመር የኮምፒውተርን ፍጥነት መጨመር ይቻላል።

 1. ኮምፒውተሮቻችንን በአግባቡ መያዝ

ኮምፒውተሮቻችንን በጥንቃቄ መያዝ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው። የኮምፒውተር መሞቅ (Overheat) ኮምፒውተሮችን በማዝገም ስራችንን ያጓትታል።  ስለሆነም ለኮምፒውተሮቻችን በሃይል እንዳይሞቅ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል።

 1. ዊንዶ መቀየር ወይም በድጋሚ መጫን

የኮምፒውተር ፍጥነት በተለያዩ ቫይረሶች ሊዳከም ስለሚችል የኮምፒውተሮቻችንን ዊንዶው በመቀየር እና ማልዌሮችን ማስወገድ   የኮምፒውተርን ፍጥነት መጨመር ይቻላል።

 1. ተጨማሪ ውጫዊ ሃርድ ዲስክ መጠቀም

የኮምፒውተሮቻችን ቦታዎች በፋይሎቿ በተጨናነቁ እና እየሞሉ ሲመጡ የኮምፒውተራችን ፍጥነት እየቀነሰ ይመጣል። ይህ በመሆኑም በተቻለ መጠን ተጨማሪ ሃርድ ዲስክ በመጠቀም የኮምፒውተራችን ቦታዎች ክፍት ማድረግ እና ፍጥነቱን ማሻሻል ይገባል።

 1. ያለትዕዛዝ ስራ የሚጀምሩ ሶፍትዌሮችን እና ፕሮግራሞች መቆጣጠር

ኮምፒውተራችንን ስናስነሳ ያለትዕዛዝ (automatically) ስራ የሚጀምሩ ሶፍትዌሮችን እና ፕሮግራሞች ይኖራሉ። እነዚህ ፕሮግራሞች መቆጣጠር እና ያለትዕዛዝ ስራ እንዳይጀምሩ ማድረግ ኮምፒውተራችንን ፍጥነት ይጨምራል።

 1. መደበኛ እና ቋሚ IP address መጠቀም

ኢንተርኔት በኮምፒውተራችን  በምንጠቀምበት ጊዜ መረጃን ለመቃረም የሚያስችለውን  መንገድ/ስርዐት  (internet protocol) ለመቀበል ጊዜ ይፈጃል። ይህንን ለማፋጠንም መደበኛ እና ቋሚ IP address በመጠቀም የኮምፒውተራችንን ፍጥነት ማስተካከል ይቻላል።

Image credit: naturalworld news.com

በሙሉቀን አንተነህ

Did you find this post helpful? Share with your friends.