የኦሎምፒክ ውድድሮች ሪከርድ ባለቤቶች

የኦሎምፒክ ውድድሮች ሪከርድ ባለቤቶች

ከዓለም ዋንጫ ጨዋታ ቀጥሎ በሁለተኝነት የሚወደደድ የዓለማችን ታላቁ ውድድር ነው የበጋ ኦሎምፒክ ጨዋታ፡፡ በያዝነውም ዓመት እ.ኤ.አ በ2016 ዓ.ም ሀምሌ 29 ቀን ይህ ውድድር በብራዚል ዋና ከተማ ሪዮ ዴጄኔሮ ለ31ኛ ጊዜ በደማቅ ስነ-ስርዓት ተከፍቶ ተጀምሯል፡፡ እኔም ለዛሬ የዋና ዋና ውድድሮች የሪከርድ ባለቤቶችን ላስተዋውቃችሁ ወደድኩ፤ ጎን ለጎንም መጪውን ውድድር በትኩረት እንድንመለከት ይረዳናል ብየ አስባለሁ፡፡

በ100 ሜ. የሩጫ ውድድር ስንጀምር በወንዶቹ የዓለማችን ቁጥር አንዱ ጃማይካዊው ዩዚያን ቦልት እ.ኤ.አ በ2012ቱ የለንደን ኦሎምፒክ 9፡.63 ሰከንድ በመግባት ሲይዝ፤ በሴቶቹ ደግሞ አሜሪካዊቱዋ ፍሎረንስ ጆይነር እ.ኤ.አ በ1988ቱ የደቡብ ኮሪያ ሲኦል ኦሎምፒክ 10.62 በሆነ ሰዓት ይዛለች፡፡ ወደ 200 ሜ. የሩጫ ጨዋታ ስንሄድ ደግሞ በወንዶቹ በተመሳሳይ የዓለማችን ቁጥር አንዱ ጃማይካዊው ዩዚያን ቦልት እ.ኤ.አ በ2008ቱ የቤይዢንግ ኦሎምፒክ 19.30 በሆነ ሰዓት በመግባት ሲይዝ በሴቶቹም በተመሳሳይ አትሌት እ.ኤ.አ በ1988ቱ የደቡብ ኮሪያ ሲኦል ኦሎምፒክ 21.34 በሆነ ሰዓት ይዛለች፡፡ በ 400 ሜ. የሩጫ ውድድር አሜሪካዊው ሚካኤል ጆንሰን እ.ኤ.አ በ1996ቱ አትላንታ ኦሎምፒክ 43.49 በሆነ ሰዓት በመግባት ሲይዝ በሴቶቹ ደግሞ ፈረንሳዊቱዋ ሜሪ ፔሪች እ.ኤ.አ በ1996ቱ የአትላንታ ኦሎምፒክ 48.25 በሆነ ሰዓት ይዛለች፡፡

ከአጭር ርቀት ውድድሮች ከፍተኛ ተከታታይ ያላቸውን ካየን አሁን ደግሞ ከመካከለኛ ርቀት ውድድሮች የተወሰኑትን እንመልከት፡፡ በ5000 ሜ. የሩጫ ውድድር ኢትጵያዊው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በ2008ቱ የቤይዢንግ ኦሎምፒክ 12፡57.82 በሆነ ሰዓት ሪከርዱን መስበር ሲችል በዛው የውድድር ዓመትና ቦታ በ10000 ሜ. የሩጫ ውድድርም 27፡01.17 በሆነ ሰዓት በመግባት የሪከርድ ባለቤት መሆን ችሏል፡፡ በሴቶቹ 10000 ሜ. የሩጫ ውድድር ደግሞ ኢትጵያዊቱዋ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በ2008ቱ የቤይዢንግ ኦሎምፒክ 29፡54.66 በሆነ ሰዓት ገብታ ሪከርዱን መስበር ችላለች(ይህ ሪከርድ በኢትዮያዊቷ አልማዝ አያና በነሀሴ 6 ቀን በተደረገው ውድድር ተሰብሯል፡፡ ሰዓቷም 29፡17፡45 ደቂቃ ነው)፡፡ በረጅም ርቀት ማራቶን ውድድር ደግሞ በሴቶቹ የኢትዮጵያ አትሌት የሆነችው ቲኪ ገላና በ2012ቱ የለንደን ኦሎምፒክ 02፡23፡07 የውድድር ሰዓት በማስመዝገብ የሪከርድ ባለቤት ለመሆን ችላለች፤ በተመሳሳይ ውድድር በወንዶቹ ደግሞ ኬኒያዊው አትሌት ሳሙኤል ዋንጂሩ በ2008 ዓ.ም በተካሄደው የለንደን ኦሎምፒክ በ2፡06፡32 በመግባት ሪከርድ ሊሰብር ችሉዋል፡፡

በአጠቃላይ ለአሁን ያልኩትን አንዳንድ የኦሎምፒክ ሪከርድ ባለቤቶች ካስተዋወኩዋችሁ የዛሬ ፅሁፌን ለሀገራችን ኢትዮጵያ አትሌቶች በብራዚል ሪዮ እየተካሄደ ባለው የ2016 ዓ.ም ኦሎምፒክ ውድድር መልካም እድልን በመመኘት ላብቃ፡፡

በሽመልስ ጌታቸው

Did you find this post helpful? Share with your friends.