በስፖርቱ ዓለም ከታዩ መልካም ተግባራት መካከል በጥቂቱ

በስፖርቱ ዓለም ከታዩ መልካም ተግባራት መካከል በጥቂቱ

ስፖርት በዓለማችን ካሉ በጎም ሆነ አስከፊ ክስተቶችን ከሚያሰተናግዱ ክንዋኔዎች ውስጥ አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ እኔም ለብዙዎቻችን ትምህርት ሰጪ ይሆናሉ ያልኩዋቸውን በስፖርተኞች የተተገበሩ በጎ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች በጥቂቱ ብናይ በሚል አንዳንዶቹን በሚከተለው ፅሁፌ ልዳስስ ሞከርኩ፡፡

  • የዓለማችን ፈጣኑ ጭ ጃማይካዊው ዩዚያን ቦልት በ2012 የለንደን ኦሎምፒክ አጋጣሚ ለአሜሪካ ብሄራዊ መዝሙር ክብር በመስጠት ሜዳ ላይ እያደረገ የነበረውን ቃለ ምልልስ በመሀል አል፡፡ ዩዚያን ቦልትም ለአሜሪካ ባንዲራ ክብር በመስጠት በትኩረት ቆሞ የተጀመረውን መዝሙር ሊያጠናቅ ችል፤ በመቀጠልም ጀምሮ የነበረውን ቃለ ምልልስ መዝሙሩ እንዳለቀ ቀጥሏል፡፡
  • በስፔን ላሊጋ የሚወዳደረው ቫሌንሲያ የእግር ስ ክለብ በኔፓል እ.ኤ.አ በ2015 ዓ.ም በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ምክንያት ለሞቱና በአደጋው መፈናቀል ለገጠማቸው የእርዳታ ማሰባሰቢያ እንዲሆን በማሰብ ስማቸውን በኔፓል በማፃፍ ጨዋታ ካካሄዱ በላ ማሊያቸው በጨረታ እንደ ተሸጠ ታውል፡፡
  • የብራዚል ብሄራዊ ቡድንና የባርሴሎና ኮከብ ኔይማር የአንድ ጃማይካዊ ህፃን ምኞት እውን ለማድረግ ከጥበቃ ሀይሎች ጋር ግጭት ውስጥ መግባቱ ይነገራል፡፡ ይህ የሆነው ብራዚል ሳውዝ አፍሪካን በሶዌቶ ካሸነፈች በላ ነበር ጨዋታው እንዳለቀ አንድ እግር ስ ደጋፊ የሆነ ህፃን የብራዚል ተጫዋቾችን ለማግኘት ወደ ሜዳ ለመግባት ከጥበቃ ሀይሎች ጋር ሲታገል ያየው ኔይማር ህፃኑን ከትግሉ በማላቀቅ ሁሉንም ተጫዋቾች እንዲያገኝና ብዙ ፎቶዎችንም እንዲነሳ ረድቶታል፡፡
  • ስዊዲናዊው ግዙፍ አጥቂ ዝላታን ኢብራሂሞቪች የ50 ሰዎችን ስም በሰውነቱ ላይ ተነቅል፡፡ በእርግጥ ዓለም ሁሉ ይህን ተጫዋች ያውቀዋል፤ ነገር ግን በረሀብ ምክንያት እየሞቱ ያሉ ብዛት ያለቸውን የዓለማችን ህዝቦች ማንም አያውቃቸውም፡፡ ዝላታን ኢብራሂሞቪችም ስለነዚህ ሰዎች በብዙዎች ዘንድ ግንዛቤ ለመፍጠር የ50 ሰዎች ያህል ስም በሰውነቱ ላይ ተነቅሶ ጎል በማስቆጠር ማልያውን አውልቆ ዓለም እንዲያየው አስችል፡፡
  • በአንድ ወቅት የቅርጫት ስ ጨዋታ ሀያል የነበረው አሜሪካዊው ማይክል ጆርዳን ስሙ ያለፍቃድ ለማስታወቂያነት በመዋሉ ለካሳ የተሰጠውን 8.9 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከቺካጎ ውጪ ለሚገኙ 23 የእርዳታ ድርጅቶች በሙሉ አስረክል፡፡
  • ፖርቹጋላዊው ጥበበኛ ክርሰቲያኖ ሮናልዶ ባሳለፍንው የፈረንጆች ዓመት የአውሮፓ ቻምፒንስ ሊግ ዋንጫን ከሪያል ማድሪድ ጋር በመሆን ማንሳቱ የሚታወስ ነው፤ ለዚህም ሮናልዶ የ600000 ዩሮ ቦነስ ተሸልሞ ይህንኑ ገንዘብ ለአንድ እርዳታ ድርጅ ሰጥል፡፡ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በኔፓልም ለተከሰተው አደጋ ባሳለፍነው ዓመት የ5 ሚሊዮን ፓውንድ እርዳታ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡
Did you find this post helpful? Share with your friends.