የአለማችን ምርጥ 10 ሀብታም ስፖርተኞች

የአለማችን ምርጥ 10 ሀብታም ስፖርተኞች

በያዝነው የፈረንጆቹ 2016 ዓ.ም ታዋቂው ፎርብስ የመገናኛ ብዙሃን በመፅሄቱ ላይ ከፍተኛ አስር ሀብታም ስፖርተኞች ስም ዝርዝርን አስፍል፡፡ የሪያል ማድሪድ ሎስ ብላንኮሱ እግር ኳስ ተጫዋች ፖርቱጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የሃብት ማማውን ከአሜሪካዊው ቦክሰኛ ፍሎይድ ሜይ ዌይዘር በያዝነው ዓመት ሊረከብ ችሏል፡፡

ፎርብስ መፅሄት የተለያዩ ታዋቂዎችን ሀብት መቆጣጠር ከጀመረበት እ.ኤ.አ ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ ዘንድሮ ለ26ኛ ጊዜ ያስቀመጣቸውን 10 የዓለማችን ሀብታም ስፖርተኞች ስም ዝርዝርን እነሆ

የሚከተሉት ቁጥሮች ጠቅላላ የዓመት ገቢያቸውን ከሜዳ ውጪ የሚያገኙትንም ጨምሮ የሚያካትት ይሆናል፡፡

በ10ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው የቅርጫት ኳስ ተጫዋቹ አሜሪካዊው ኮቢ ብሪያንት በዓመት በሚያስገባው የ50 ሚሊዮን ዶላር ክምችት ሲሆን፤ በአንደኝነት ላይ የተቀመጠው ደግሞ ጥበበኛው የእግር ኳስ ተጫዋቹ ፖርቱጋላዊው ክርስትያኖ ሮናልዶ በ88 ሚሊዮን ዶላር ሀብት ነው፡፡ የሚከተለው ሳጥን ፎርብስ መፅሄት ያስቀመጠውን ሙሉ ደረጃ ያስመለክተናል፡፡

ደረጃ ስፖርተኛ የስፖርት አይነት የሀብት መጠን በዶላር
1ኛ ክርስቲያኖ ሮናልዶ እግር ኳስ 88 ሚሊዮን
2ኛ ሊዮኔል ሜሲ እግር ኳስ 81.4 ሚሊዮን
3ኛ ልብሮን ጄምስ ቅርጫት ኳስ 77.2 ሚሊዮን
4ኛ ሮጀር ፌደረር ሜዳ ቴኒስ 67.8 ሚሊዮን
5ኛ ኬቪን ዱራንት ቅርጫት ኳስ 56.2 ሚሊዮን
6ኛ ኖቫክ ጆኮቪች ሜዳ ቴኒስ 55.8 ሚሊዮን
7ኛ ካም ኒውተን የአሜሪካ እግር ኳስ 53.1 ሚሊዮን
8ኛ ፊል ሚኬልሰን ጎልፍ 52.9 ሚሊዮን
9ኛ ጆርዳን ስፒዝ ጎልፍ 52.8 ሚሊዮን
10ኛ ኮቢ ብሪያንት ቅርጫት ኳስ 50 ሚሊዮን
Did you find this post helpful? Share with your friends.