ማጨስ ለማቆም የሚረዱ ነጥቦች

ማጨስ ለማቆም የሚረዱ ነጥቦች

  1. ለምን ለማቆም እንደወሰንክ ጠንቅቆ ማወቅ

የአብዛኛው አጫሽ ምክንያት ተቀራራቢ ቢሆንም ሁሉም ሰው እንደ ማንነቱና አስተሳሰቡ የራሱ ልዩ ምክንያት ሊኖረው ይችላል፡፡ ምክንያትህን በወረቀት ላይ አስፍረህ አስቀምጥ፤ አዲስ ሀሳብ ስታገን ጨምርበት፡፡ ወረቀቱን ይዘህ ብትቀሳቀስ ጥርጣሬ በተሰማህና የማጨስ ስት በሚፈታተንህ ጊዜ ምክነያቶችህን በመከለስ ራስህን ለማትጋት ይረዳሀል፡፡

  1. አእምሮን መቆጣጠር

ሱስህን የመግታት ጉዞህን የጀመርክ ሰሞን “አንድ ብቻ አጭስ” የሚል ስሜት ሊፈታተንህ ይችላል፡፡ እንዲያውም የመጀመሪያዎቹ አንድ ወይም ሁለት ሳምንታት አእምሮህ ከማጨስ ውጪ ያለጉዳይ ማሰብ የሚችል ላይመስልህ ሁሉ ይችላል፡፡

ሱስ ከሰውነታችን ይልቅ አእምሯችንን የመቆጣጠር ኃይል አለው፡፡ በመሆኑም ሱስህን ለማቆም ስትወስን አእምሮህ የሙሉ ጊዜው እንዳታቆም ሃሳብ ማመንጨት ይሆናል፡፡ ይህን ማወቁ ሂደተን ያቀልልሃል

  1. እንድታጨስ የሚፈታተኑህንነገሮች ለማሸነፍ ዝግጁ መሆን

ሳታስበው እንድታጨስ የሚፈታተኑ ስሜቶች ሊፈጠብህ ይችላሉ፡፡ እነዚሀን ስሜቶች መቆጣጠር እጅግ አዳጋች ሊሆን ቢችልም በነዚህ መንገዶች መቋቋም ትችላለህ

እራስን ማረሳሳት፡ ይሄ “ አጭስ አጭስ” የሚል ስሜት ለመርሳት እራስህን ነስ ወይም በተለያዩ እንቅስቃሴዎች መጥመድ

ስናኮች መብላት፡ ማጨስ በሚያምርህ ጊዜ የተለያዩ ብስኩቶች፣ ማስቲካ ወይም ፍራፍሬ በመመገብ ራስን ለማረሳሳት መሞከር

አልኮል ስለመጠጣት በፍጹም እንዳታስብ፡፡ መጠጥ ቤትም ሆነ መናቸውም በብዛት የሚጨስባቸው ቦታዎችን ማዘውተርራህን ለጭንቀት መዳረግ ነው፡፡ ገና ማጨስ ማቆምህ እንደመሆኑ መጠን ከእንደዚህ አይነት እንቅስቃሴዎች መቆጠብ አለብህ፡፡፡ የሚጨስበት ቦታ መገኘት የማረብሽህ ጊዜ መጣልና እስከዛው ታገስ

ማጨስ ለማቆም በምታደርገው ትረት የሚያበረታቱህ ሰዎች ዙሪያህ ቢኖሩ መልካም ነው፡፡ ቤተሰቦችህ እነዲሁም ጓፈኞችህ በጥሩ መልኩ ሊያግዙህ ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን የመታልፍበትን መንገድ ላይረዱት ልሚችሉ እንዳንተው ለማቆም በቆረጡ ወይም ያቆሙ ሰዎች  መክበብ ጠቃሚ ነው፡፡

  1. ራስን ማድነቅ/ መሸለም

ሳታጨስ አንድ ቀን ማሳለፍ ማለት ትልቅ ስኬት ነው፡፡ ቀስ በቀስ ያለ ሲጋራ እንዴት መኖር አንደምትችል እራስህን እያስተማርክ ነው ማለት ነው፡፡

Did you find this post helpful? Share with your friends.